693 የህግ ታራሚዎች በይቅርታና በምህረት ተለቀቁ

0
38

693 የህግ ታራሚዎች በይቅርታና በምህረት ተለቀቁ

693 የህግ ታራሚዎች በይቅርታና በምህረት መለቀቃቸውን የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር አስታወቀ፡፡

በህገ- መንግስታዊ ስርአቱ ላይ የሚደረግ ወንጀል፣ የጦር መሳሪያን ይዞ ለእርስ በእርስ ጦርነት ማነሳሳት፣ በሀገር ክደት፣ በስለላ ወንጀልና ሌሎች መሰል ወንጀሎች ተከሰው በቀጠሮ የነበሩ እንዲሁም የተፈረደባቸው 209 ታራሚዎች ከእስር እንዲለቀቁ ተደርጓል፡፡

በተጨማሪም በማረሚያ ቤት ቆይታቸው ባሳዩት መልካም ስነ- ምግባር በተለያዩ ወንጀሎች ተከሰው በማረሚያ ቤት ለነበሩ 484 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ በማድረግ ከማረሚያ ቤት እንዲወጡ መደረጉ ተገልጿል፡፡

በአጠቃላይ 693 የህግ ታራሚዎችን በምህረትና በይቅርታ ከማረሚያ ቤት እንዲወጡ መደረጉን የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር አስታውቋል፡፡

ለታራሚዎቹ የተደረገው ምህረትና ይቅርታ የምረት አዋጁ ከፀደቀ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የተደረገ ነው ተብሏል፡፡

ህብረተሰቡም ከእስር የተለቀቁትን ታራሚዎች ወደ ማህበረሰቡ ተቀላቅለው መኖር እንዲችሉ ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባውና ታራሚዎችም በማረሚያ ቤት ቆይታቸው ያሳዩትን መልካም ስነ- ምግባር ወደ ህብረተሰቡ ሲቀላቀሉ ሊቀጥሉ እንደሚገባም ተገልፅዋል፡፡

የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር የህዝብ ግኙነት ፅ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here