በአዲስ አበባ የአቃቂ ወንዝ ሞልቶ የትራንስፖርት መስተጓጎል አስከተለ

0
89


በአዲስ አበባ የአቃቂ ወንዝ ሞልቶ የትራንስፖርት መስተጓጎል አስከተለ

በአዲስ አበባ ዛሬ ማለዳ ላይ የአቃቂ ወንዝ ሞልቶ የትራንስፖርት መስተጓጎል እና በሰው ላይ አደጋ ጋርጦ እንደነበር የአዲስ አበባ ከተማ እሳትና ድንገተኛ አደጋ መቆጣጠርና መከላከል ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

ዛሬ ነሐሴ 16፣20110 ከማለዳው 12፡15 ላይ የአቃቂ ወንዝ ሞልቶ በመገንፈሉ ሀያ ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ ቅጥቅጥ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ በውሃ ሙላት ተይዞ አደጋ ላይ የነበሩ ሰዎች ህይወት በአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ማትረፍ መቻሉን ባለስልጣኑ አስታውቋል፡፡

በውሃ ሙላቱ ህይወታቸውን ለማትርፍ ተሳፋሪዎች በመኪናው አናት ላይ ለመቆየት ተገደዋል፡፡

የተሳፋሪዎቹን ህይወት ለማትረፍ የአየር ኃይል ሄሊኮፍተርን ጨምሮ የአዲስ አበባ ከተማ እሳትና ድንገተኛ አደጋ መቆጣጠርና መከላከል ባለስልጣን ባለሞያዎችና ዋናተኞች ልዩ ልዩ ማሽነሪዎችን በመታገዝ ያደረጉት ርብርብ እንደተሳካቸው የባለስልጣኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለኢቢሲ አስታውቀዋል፡፡

ሰዎቹን ለተጨማሪ ምርመራና ህክምና ወደ አቃቂ ጤና ጣቢያ መላካቸውንም አመልክተዋል፡፡
በአደጋው በሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩም ተመልክቷል፡፡
ምንጭ፡EBC

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here