ጦርነቱ እየተካሄደ ያለው ከአብዲ ኢሌ የሠለጠኑ ገዳይ ወታደሮችና መቀሌ ከመሸጉ የተባረሩ ጄኔራሎች ጋር ነው፡፡

0
58

ጦርነቱ እየተካሄደ ያለው ከአብዲ ኢሌ የሠለጠኑ ገዳይ ወታደሮች ጋር ብቻ አይደለም፡፡ እነሱን በምክርና አብረው ከነሱ ጋር የተሰለፉ 5 የህወኃት ኮርኔሎችና ጄኔራል ኳርተርና ሌሎች ከመከላከያ የተሰናበቱ ጄኔራሎች በምክር ከመቀሌ ሆነው እየመሩ ይገኛሉ፡፡ አሁን ደግሞ ኦብነግና አልሸባብ በጦርነቱ ለመሳተፍ በዝግጅት ላይ ናቸው፡፡

አብዲ ኢሌ ዛሬ የሀገር ሽማግሌዎችን በመጥራት እገነጠላለሁ የሚለው ወሬ በጠላቶቹ እንደተወራበትና እሱም ስልጣኑን እንደሚያስረክብ እነሱም ለሰላም መትጋት እንዳለባቸው ገልጿል፡፡ አያይዞም የመከላከያ ሠራዊት ወደከተማው እንዲገቡ መፍቀዱን ተናግሯል፡፡ ነገር ግን ይሄ ሰውዬ አሁን የተናገረውን ከሰዓት በኃላ ስለሚቀይረው ያለውን ለማመን አይቻልም፡፡ ጠላቶቹም ማን እንደሆኑ ሳይናገር በደፈናው አልፎታል፡፡

ዛሬ ረፋድ ላይ በጅግጅጋ የተቃጠለውን ቤተክርስትያን ሲጎበኝ ምዕመናኑ ሌባ ሌባ ሲሉት ግዜ ድንብርብሩ ወጥቶ አካባቢውን ለቆ በመጣበት ፍጥነት ተመልሶ ሄዷል፡፡

በጅግጅጋ ገራድ ውልዋል ኤርፖርት የመከላከያ ሠራዊት ቁጥር ወደ ሦስት ሺህ ደርሷል፡፡ በሶማሊያ ግዛት በለድዌይኔ የነበረው መከላከያ ሠራዊት ወደ አገር ቤት በመመለስ ድንበር አካባቢ ጥበቃ ማድረግ ጀምሯል፡፡

የሱማሌ ክልል ሽማግሌዎችና ምሁራን ከመከላከያ ጋር ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን እየገለፁ ነው፡፡

አብዲ ኢሌ አልተያዘም! ውዥንብሩ የመጣው መከላከያ ሠራዊታችን ሕዝቡ እንዳይጨረስ ከመፈለግ አኳያ በማፈግፈግ ወደ ጦር ሠፈሩ በመመለሱ ነው፡፡ አብዲ ኢሌ ይህን በመጠቀም ለመደበቅ በቅቷል፡፡ የነበረበትን ቦታ ስላልታወቀ ሰዎች የተለያዩ ሀሰተኛ መረጃዎች ያወጡ ነበር፡፡

ረጆ ተይዟል የሚለውን መልዕክት ያስተላለፈችው የአብዲ ኢሌ ደጋፊዎች ተስፋ ቆርጠው ወደጥፋት እንዳይገቡ ለመከላከል ነበር፡፡ አሁን የእውነታው ሰዓት ስለተቃረበ ሁሉም እውነቱን እንድያውቁ ረጆ ትሻለች፡፡

በነገራችን ላይ ሌላው ኢትዮጵያዊ እንዲያውቀው የሚንፈልገው ጦርነቱ እየተካሄደ ያለው ከአብዲ ኢሌ የሠለጠኑ ገዳይ ወታደሮች ጋር ብቻ አይደለም፡፡ እነሱን በምክርና አብረው ከነሱ ጋር የተሰለፉ 5 የህወኃት ኮርኔሎችና ጄኔራል ኳርተርና ሌሎች ከመከላከያ የተሰናበቱ ጄኔራሎች በምክር ከመቀሌ ሆነው እየመሩ ይገኛሉ፡፡ አሁን ደግሞ ኦብነግና አልሸባብ በጦርነቱ ለመሳተፍ በዝግጅት ላይ ናቸው፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here