ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በቤጂንግ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

0
42

ነህሴ 26፣2010

የቻይና አፍሪካ ፎረም ላይ ለመሣተፍ ወደ ቻይና ያቀኑት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው፡፡

በቤጂንግ አለም አቀፍ ኤርፖርትም ሲደርሱ የቻይና የውጭ ጉዳይ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታና ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

ዶ/ር ዐቢይ በቻይና ቆይታቸው በፎረሙ ከመሣተፍ ጐን ለጐን የተለያዩ ውይይቶችን ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በቤጂን የሚደረገው የቻይና አፍሪካ የትብብር ፎረም ቻይና ከአፍሪካ አህጉር ጋር ያላትን ግንኙነት ይበልጥ የምታጠናክርበት እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡

እ.ኤ.አ በ2ዐዐዐ ዓም የተጀመረው የቻይና አፍሪካ ትብብር ፎረም በየ3 አመቱ የሚካሄድ ሲሆን እስካሁን ኢትዮጵያን ጨምሮ በ3 የአፍሪካ አገራት ተካሂዷል፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here