ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ ነገ ለሃገር ውስጥ ጋዜጠኞች መግለጫ ይሰጣሉ

0
10


አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 18 ፣ 2010 የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ነገ ለሃገር ውስጥ ጋዜጠኞች በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ማብራሪያ ይሰጣሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ነገ ከሰዓት ከ9: 00 ሰዓት ጀምሮ ከሀገር ውስጥ ጋዜጠኞች በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ እንደሚሰጡ፥ የጠቅላይ ሚኒስትር ልዩ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ፍጹም አረጋ በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል።

ዶክተር ዐቢይ አህመድ የዛሬ አራት ወር የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን መሾማቸው ይታወሳል።

በነገው ዕለት ከሃገር ውስጥ ጋዜጠኞች ጋር የሚያደርጉት ቆይታም፥ ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ የመጀመሪያቸው ይሆናል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here