ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የአሜሪካ ጉብኝታቸውን አጠናቀው አዲስ አበባ ገቡ

0
23

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የአሜሪካ ጉብኝታቸውን አጠናቀው አዲስ አበባ ገቡ
*************************************************************************
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በአሜሪካ ለአንድ ሳምንት የነበራቸውን ቆይታ አጠናቀው አዲስ አበባ ገቡ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ግንቡን እናፍርስ፣ ድልድዩን እንገንባ” በሚለው ዘመቻቸው በአሜሪካ ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ጋር በዋሽንግተን ዲሲ፣ በሎስ አንጀለስና ሚኒሶታ ውይይት አድርገዋል፡፡

በስደት ካሉ ከተለያዩ ፖለቲካ ኃይሎችና የሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብት አራማጆችም ጋር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ውይይት አድርገዋል፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በአገር ውስጥና በውጭ በስደት በልዩነት ሲኖሩ የነበሩ ሁለቱ ሲኖዶሶች እርቅ ባወረዱበት መድረክም ላይ እና በኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች አለም አቀፍ የበድር ጉባኤ ላይም ተካፍለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከአለም ባንክና የአለም አቀፉ ገንዘብ ተቋም አመራሮችም ጋር የኢትዮጵያን የምጣኔ ሀብት ማሻሻያ መደገፍ በሚችሉባቸው አማጮች ላይም መክረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አዲስ አበባ ሲገቡ አራተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ፓትርያርክ አባ መርቆሪዮስ እና አበው ሊቃነ ጳጳሳትም አብረው ከመጡበት አንድ አውሮፕላን ወርደው ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here