በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የሚመራ የኢትዮጵያ የልዑካን ቡድን በኤርትራ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ አስመራ ገብቷል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና ልኡካቸው አስመራ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የልዑካን ቡድኑ ከኤርትራ መንግስት ጋር የሁለቱን አገራት ጥቅም ያማከለ ሁሉን አቀፍ ትብብር ላይ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡