የኢትዮጵያ አየር መንገድ የዛምቢያውን አየር መንገድ በ30 ሚሊዮን ዶላር ዳግም ስራ ሊያስጀምር ነው

0
19

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የዛምቢያውን አየር መንገድ በ30 ሚሊዮን ዶላር ዳግም ስራ ሊያስጀምር ነው
ነሀሴ 14፣2010

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተዘግቶ የቆየውን የዛምቢያውን አየር መንገድ በ30 ሚሊዮን ዶላር መነሻ ኢንቨስትመንት ዳግም ለማስጀመር ከዛምቢያ የልማት ኤጄንሲ ጋር ስምምነት ተፈራረመ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና የዛምቢያ የኢንዱስትሪ ልማት ኮርፖሬሽን በጋራ በሰጡት መግለጫ በስምምነቱ ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ተዘግቶ የቆየውን የዛምቢያ አየር መንገድ መልሶ ለማቋቋምና እ.አ.አ በ2028 አስራ ሁለት አውሮፕላኖችን ለማንቀሳቀስ ያስችለዋል ብለዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዛምቢያ አየር መንገድ 45 ከመቶ ድርሻ መግዛቱ ይታወሳል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የማላዊ አየር መንገድን ለማስተዳደር እ.አ.አ በ2013 ስምምነት ላይ መድረሱ ይታወሳል።

የአየር መንገዱ ባለፈው ግንቦት በዘርፉ አብሮ ለመስራት ቻድ፣ ጅቡቲ፣ ኢኩዋቶሪያል ጊኒ እና ጊኒ ጋር ድርድር መጀመሩን የገለጸ ሲሆን፣ አየር መንገዱ የሞዛምቢክ አየርን መንገድን ሙሉ በሙሉ ለመረከብ እቅድ እንዳለው ገልጿል፡፡

ምንጭ:- ሮይተርስ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here