የአሜሪካው ሴናተር ጆን ማኬይን በ81 አመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

0
28

የአሜሪካው ሴናተር ጆን ማኬይን
የአሜሪካው ሴናተር ጆን ማኬይን በ81 አመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

ከ30 አመት በላይ የአሪዞና ሴናተር በመሆን ያገለገሉት ጆን ማኬይን በ81 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል፡፡

እኤአ ከሃምሌ 2017 ጀምሮ በከፍተኛ ሁኔታ በአንጎል ካንሰር ህመም ሲሰቃዩ የቆዩ ሲሆን በሚያዚያ ወርም የአንጀት ኢንፌክሽን ቀዶ ህክምና ማድረጋቸውን የሲጂቲን ዘገባ ያመለክታል፡፡
ቤተሰባቸው አርብ እለት ማኬይን የካንሰር ህክምናውን እንዳቋረጡ አስታውቀው ነበር ብሏል ዘገባው፡፡
ከሞታቸው በኋላ ትናንት በወጣው መግለጫ “አሜሪካን በታማኝነት ላለፉት 60 አመታት አገልግለዋል” ተብሏል፡፡
ቀብራቸው በአናፖሊስ ሜሪላንድ ከመከናወኑ በፊት በዋሽንግተን ብሄራዊ ካቴድራል አሸኛኘት እንደሚደረግ ቤተሰቦቻቸው መግለጻቸውም ዘገባው ጠቁሟል፡፡
የቀድሞው የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ፣ጆርጅ ደብሊው ቡሽና ምክትል ፕሬዝዳንት ጆን ባይደን የሃዘን መግለጫ እንደሚያስተላልፉም ይጠበቃል ተብሏል፡፡

ሴናተር ማክኬይን ባይሳካላቸውም እኤአ በ2008 ለአሜሪካን ፐሬዝዳንትነት የተወዳደሩ ሲሆን የአሁኑን የአሜሪካ ፐሬዚዳንት በመተቸት እንደሚታወቁም ዘገባው አስታወሷል፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here