የቤኒሻንጉል ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት ለ2011 በጀት ዓመት 3.6 ቢሊዮን ብር አፀደቀ፡፡

0
29

የቤኒሻንጉል ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት ለ2011 በጀት ዓመት 3.6 ቢሊዮን ብር አፀደቀ፡፡
የክልሉ ምክር ምክር ቤት ላለፉት ሶስት ቀናት ባካሄደው 5ኛ ዓመት 7 መደበኛ ጉባኤው የክልሉን የ2011 በጀት በጀትና የተለያዩ ሹመቶችን በማጽደቅ ጉባኤውን አጠናቋል፡፡
ለተያዘው በጀት ዓመት የፀደቀው የ3.6 ቢሊዮን ብር በጀት ከባለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር በ147ሚሊዮን ብር ቅናሽ አሳይቷል።
ምክር ቤቱ የተለያዩ ቢሮ ኃላፊዎችንና ቋሚ ኮሚቴዎችንና ሹመትንም አፅድቋል፡፡በዚሁ መሰረት ፡
1. አቶ አበራ ባያታ የክልሉ ም/ርዕሰ መስተዳድር እና የስራና ከተማ ልማት ቢሮ ኃላፊ
2. አቶ ኢስያቅ አብዱልቃድር የአካባቢ ደንና መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ቢሮ ኃላፊ
3. አቶ አወቀ አይሸሽም የክልሉ ገቢዎች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክትር
4. ወ/ሮ ሃጅራ ኢብራሂም የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ
5. አቶ አሸሪፍ አሀጅኑር የፐብሊክ ሰርቪስ ሰው ሃይል ልማት ቢሮ ኃላፊ
6. አቶ ዘላለም ጃለታ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ
7. አቶ ፀጋዩ ተሰማ የወጣቶችና እና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ
8. አቶ ቶማስ ኩዊ የመንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ
9. አቶ ሙሳ አህመድ የአስ/ጸ/ማ/ጉ ቢሮ ኃላፊ እንዲሆኑ የቀረበውን ሹመት በ 2 ድምፅ ተዓቅቦና በአብላጫ ድምጽ በም/ቤቱ አባላት ፀድቋል፡፡ምክር ቤቱ የ7 ዳኞችን ሹመት በማፅደቅ ቃለ መሃላ እንዲፈፅሙ አድርጓል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here