የቀድሞው የሱማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አብዲ መሐመድ ዑመር ፍርድ ቤት ቀረቡ

0
52

የቀድሞው የሱማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አብዲ መሐመድ ዑመር ፍርድ ቤት ቀረቡ
የቀድሞ የኢትዮጵያ ሱማሌ
አቶ አብዲ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተረኛ ችሎት ነው የቀረቡት፡፡

አቶ አብዲን ጨምሮ አራት ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ የቀድሞ የክልሉ የሴቶችና ሕፃናት ቢሮ ኃላፊ ራህማ ማህሙድ ሀይቤ፣ የቀድሞ የክልሉ የዳያስፖራ ቢሮ ኃላፊ አብዱረዛቅ ሳኒ እና የቀድሞ የክልሉ የመስኖ ልማት ቢሮ ኃላፊ ሱልጣን መሐመድ ይገኙበታል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ የተጠረጠሩበት ወንጀል ዘርና ብሔርን ለይተው የክልሉን ወጣቶች አስታጥቀው ለበርካቶች ሞትና መፈናቀል፣ እንዲሁም ለሃይማኖት ተቋማት ውድመት ምክንያት ሆነዋል በሚል ነው፡፡

ፖሊስ ለምርመራ 15 ቀን ጠይቋል፡፡

ሁሉም ተጠርጣሪዎች የዋስትና መብታቸው እንዲከበር ጠይቀዋል፣ ፖሊስ ለምርመራ የጠየቀው ጊዜ በዝቷል፣ ፖሊስ እስከ አሁን ቃላችንን አልተቀበለም ነገር ግን ከተያዝን 48 ሰዓት አልፏል የሚሉ ጥያቄዎችን ጠይቀዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here