የሰኔ 16ቱን የቦንብ ጥቃት በተመለከተ የኤፍ ቢ አይን የቴክኒክ ምርመራ አጠናቆ ለማቅረብ የጠየቀው ፖሊስ 14 ቀን ተፈቀደለት

0
38

የሰኔ 16ቱን የቦንብ ጥቃት በተመለከተ የኤፍ ቢ አይን የቴክኒክ ምርመራ አጠናቆ ለማቅረብ የጠየቀው ፖሊስ 14 ቀን ተፈቀደለት

የፌደራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተረኛ ችሎት በሰኔ 16ቱ የቦንብ ጥቃት የኤፍ ቢ አይን የቴክኒክ የምርመራ ውጤትን አጠናቆ ለማቅረብ ፖሊስ የጠየቀውን 14 ቀን ተጨማሪ ጊዜ ለመጨረሻ ጊዜ ፈቀደ።

ችሎቱ በዚህ የቦንብ ጥቃት በማስተባበርና በተሳትፎ የተጠረጠሩ በሁለት የምርመራ መዝገብ የስድስት ግለሰቦችን ጉዳይ ተመልክቷል።

በየነ ሩዳ እና አብዲሳ መገርሳ በአንደኛው መዝገብ የተጠቀሱ ሲሆን በተለይም በየነ ሩዳ በሌሎች የምርመራ መዝገብ ከተጠቀሱ ግብራበሮቹ ጋር በመሆን ጥቃቱን አስተባብሯል በሚል ነው የተጠረጠረው።
አብዲሳ መገርሳም በዕለቱ ጥቃቱን በተመለከተ ለግብራበሮቹ ሪፖርት ሲያደረግ መያዙን የፖሊስ የምርመራ መዝገብ የሳያል።

አብዲሳ ቀነኒ፣ ደሳለኝ ተስፋዬ ፣ጌቱ ግርማ፣ ህይወት ገዳና ባህሩ ቶላ ደግሞ በሁለተኛው የምርመራ መዝገብ የተካተቱ ናቸው።

ከነዚህ መካከል ህይወት ገዳ የአእምሮ ህመምተኛ መሆኗ በህክምና በመረጋገጡ ክሷ ተቋርጧል።

በዚህ መዝገብ ጌቱ ግርማ ጥቃቱን ሲያስተባብር እንደነበር ፖሊስ ገልጿል።
የግለሰቡ ቤት ሲበረበርም ቦንብ መገኘቱንም ፖሊስ አስታውቋል ።

ፖሊሲ የኤፍ ቢአይን የቴክኒክ የምርመራ ውጤትን እና ተጨማሪ የምስክሮችን ቃል ለማጠናቀር 14 ቀን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ጠይቋል።

የተጠርጣሪ ጠበቆች በበኩላቸው ግለሰቦቹ ባልፈፀሙት ወንጀል እየተጠየቁ ነው ፤ፖሊስ እስካሁን በተሰጠው ጊዜ አዲስ ነገር አላቀረበም፤ የጠየቀው ተጨማሪ ጊዜ የተገቢ አይደለም ፤በሚል የዋስትና መብት ይከበር ጥያቄ አቅርቧል።

የግራ ቀኙን ክርክር የመረመረው ችሎቱ የተጠርጣሪዎችን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ በማድረግ የምስክሮችን ቃልና የኤፍቢአይ የምርመራ ውጤትን ለመመልከት የመጨረሻ ጊዜ በማለት በፖሊስ የተጠየቀውን 14 ቀን ፈቅዷል።

ፖሊስ ከቀጠሮው ሁለት ቀን አስቀድሞ የምርመራ መዝገቡን እንዲያቀርብም ትዕዛዝ ሰጥቷል።
ምንጭ፡EBC

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here