ዕውን በትግራይ ሰላም ሰፍኗል? (ወንድሙ መኰንን፣ ከኢንግላንድ)

0
81

ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ

ሰሞኑን ከዘጠኙ ክልሎችና ከሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ 22 የሰላም ጥሪ ያነገቡ፣ የሰላም አምባሳደሮች የተባሉ እናቶች፣ በኢትዮጵያ ልዩ ልዩ ቦታዎች በመገኘት ሰላምን ለመስበክ ጉዞ ጀምረዋል። የመጀመሪያ ጉዞአቸው ኅዳር 17 ቀን 2011 ዓመተ ምሕረት ወደአማራው ክልል በማምራት ተጀመረ። በባሕር ዳር የተደረገላቸው አቀባበል ልዩ ነበር። ከተናጋሪዋ የያንዳንዱ ዐረፍተ ነገር በኋላ አድማጩ በስሜት እያጨበጨበ ነበር ዓላማቸውን ሲደግፍ የተስተዋለው። አማሮቹ፣ ሰላም እንደደፈረሰባቸው ያውቃሉ። ሰላማቸውን ማን እንደነሳችውም፣ ልጆቻቸውን ለጭዳ ያቀረበባቸውንም የማፊያ ቡድንን አጣርተው ያውቁታል። አማራነት ዋጋ ያስከፍላል። የእነዚህን የሰላም አምባሳደር የእናቶችን ለቅሶ ይጋራቸዋል። በተለይ የሀረሪ ክልል የተወከይዋ አምባሳደር “እኛ አምባሳደሮች የ50 ሚሊዮን እናቶች ጥያቄ በመቀበል በየክልሉና ከተማ አስተዳደሮች እየዞርን ነው” እያሉ በዕምባ በታጀበ ንግግር ሲያደርጉ፣ የባሕርዳር ኗሪ በዕንባ እያጀባቸው ነበር ተልዕኮአቸው እንዲሳካላቸው የተመኘላቸው።“ዘርን መሰረት ያደረገ ጥላቻ እንዲቆም እንፈልጋለን” የሚሉት ተልዕኮ እንደሳካላቸው እየተመኘው ወደ ትግራይ ሸኝተዋቸዋል። ትግራይ ሲደርሱ ነገሩ ሌላ ሆነ[1]

Dr. Debretsion Gebremichael.

እነዚህ የሰላም አምባሳደሮች ግን መቀሌ ሲደርሱ፣ አቀባበላቸው የቀዘቀዘና “ምን ልታደርጉ መጣችሁ?” የሚል ዓይነት አቀባበል ይመስል ነበር። ተቀብለው ያነጋገሯቸው፣ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረፂዮን ገብረ ሚካኤል ነበሩ። ለመሆኑ ዋናው አስተዳዳሪ ማን ናቸው? አይታዩም፣ አይሰሙም። የምናየው የምንሰማው ሁልጊዜ ደበረፂይንን ነው። ደብረጽዮን ደሞ ምክትል ናቸው። ኧረ የዋናው ያለህ! ዋናው የቀን ጅብ ሁነው ይሆን የሚደበቁት?

ዶክተር ደብረፂዮን ገብረ ሚካኤል ባደረጉት ንግግር፥ የሰላም አምባሳደር ሆናችሁ የመጣችሁበት ትግራይ ክልል የሰላም አከባቢ ነው ብለዋለዋቸው አረፉ። ምክትል ርዕሰ መሰዳደሩ “ሰላም የሌለው ሌሎች ክልል ነው” በማለት አፋቸውን ሞልተው ተናግረዋቸዋል። ዕውን ያላላቀሰች የትግሬ እናት ትኖር ይሆን? ዕውን ትግራይ ሰላም የሰፈነባት ክልል ናት?

መቼም ዶክተር ደብረፂዮን ግርም የሚሉ ገጸ ባሕርይ ናቸው። መቀሌ ሲሄዱ በነዶክተር ዐቢይ በሚመራው ለውጥ  አራማጆች ላይ ጦርነት ያውጃሉ፣ ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ፣ የለውጡ ደጋፊ እንደሆኑና፣ መቀሌ የሌቦቹ መሸሸጊያ እንደማትሆን ይነግሩናል። ምን ዓይነት ተዋናይ ናቸው ጃል? አራዳ መኮኑ ነው?

የትግራይ ክልል ምንም ሰላም እንዳልሰፈነባት፣ ግጥም አድርገው ዶክተሩ ያውቃሉ። የትግራይ ተስፋፊዎች፣ ወልቃይትን፣ ሑመራንና ጸለምትን ከጎንደር ነጥቀው ሕዝቡን እያመሱት ምን ሰላም አለ? ወልቃይት ትግራይ ከሆነች፣ የወልቃይቴዪቱ እናት ልጇን እየታረደባት ደም-ዕንባ ስትረጭ ያ የሰላም ምልክት መሆኑ ነው? የልጇ ደም የሚፈሰው የትግራይን ሰላም ለማስፈን ነው? ይኸ ነው የነሱ ሰላም? ራያን ከወሎ ነጥቀው በየቀኑ የራያይቱ እናት ልጇ በትግራይ ልዩ ኃይል እያታረደባት ደም-ዕምባዋን እየረጨች፣ ሰላም አለ ይሉናል ዶክተረ ደብረፂዮን? የተግራይ ተስፋፊዎች፣ በማፊያው ቡደን በሕውሀት እየተመሩ፣ የኃብት ዘረፋ ርብርቦሽ፣ በየቀኑ ከአፋሮቹ ጋር የሚደረገው ትንቅንቅ የሰላም ምልክት ነው? በዚህ የጥቂቶች ጥቅም ማስጠበቂያ ስንቷ የትግራይ እናት ናት ልጇን አጥታ አጨብጭባ መርዶ የተቀመጠችው? የትግራይ ሕዝብ ተተብትቦ በማፊያዎቹ ተይዞ ለጊዜው የሆዱን በሆዱ አስቀምጦ እንደፈለጉት ስለሚታዘዝላቸው፣ ሰላም መስሏቸው ይሆን? ትግራይ ከሥሯ እሳተ-ገሞራው እየተፍለቀለቀ ነው። ወንጀለኞቹ መቀሌ እስከተሸሸጉ ድረስ ትግራይ ሰላም የላትም፣ አይኖራትም።

ምናልባት፣ ኢትዮጵያን ለ27 ዓመታት ሲያምሷት የነበሩት፣ የማፊያ መሪዎች፣ በአሁኑ ሰዓት መቀሌ መሽገው፣ ዙሪያዋን በከባድ መሣሪያ በማስጠበቅ፣ ለራሳቸው ሰላም የሰፈነላቸው መስሏቸው ይሆናል እንጂ፣ ትግራይስ ባሩድ ላይ የተቅመጠች ማሰሮ ናት። ሰላሟ የሚረጋገጠው፣ ረግጦ አፍኖ የያዛት ማፈሪያ አፓርታይድ ወያኔ ሲወድም ብቻ ነው።

ሲፈጠሩ፣ ወያኔዎች መች ሰላም ተውጦላቸው ያውቃል? “ጦርነት መሥራት እንችላለን” እያሉ አይደል የሞፎክሩብን? ወያኔዎች እስካሉ ድረስ ምንም ሰላም አይኖርም። 27 ዓመት ሙሉ አገሪቱን፣ ኢትዮጵያን ሲመዘብሯት፣ ሲዘርፏት፣ ሲያራቁቷት፣ አገር ቆርሰው ለጎረቤትና ለዓለማቀፍ አግሮ-ኮንግላሜሬትስ ሲቸበችቧት፣ በየቦታው ደም እያፈሰሱ ሰላም ሲነሷት፣ “ኧረ ዕርቀሰላም ይውረድ” እያለ የሚጮኸውን ሕዝብ “አታሟርቱ! አገሪቱ ከምንጊዜም በላይ በኛ ዘመን ሰላማዊ ናት” እያሉ እራሳቸውን ሲያሞኙ፣ ቄሮና ፋኖ በየቦታው በባዶ እጁ ሲፋለማቸው የነለማ-ገዱ ቲም መሐላቸው ብድግ ብለው የቆሙበትን ምንጣፍ ከእግራቸው ሥር ሲመዙባቸው ተንሸራትተው ይኸውና ምድረ ወንጀለኛ ፋሺስት ሁሉ መቀመቅ፣ ይቅርታ፣ መቀሌ ወርደዋል። የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ፣ አንቀው የያዙት የትግራይ ሕዝብም እንደወንድሞቹ ምንጣፋቸውን ከእግራቸው ሥር ሲስብባቸው ሳይስቡት እንጦርጦሮስ ይወርዷታል። እያንዳንዳቸው በገነቧት ወህኒ ቤቱ ይታጎሯታል። “ኢትዮጵያን ዕድሜ ልካችንን ረግጠን እንገዛታለን” ያሏት ፉከራ በ27 ዓመት ከበረዶ የቀዘቀዘ ውሀ ተቸልሶባታል። አሁንም ትንሿን ትግራይን ትልቅ አድርገን ከኢትዮጵያ ገንጥለን የትግራይን ሪፓብሊክ እንመሠርታለን” የምትለዋ ቅዠታቸውም እንደጉም ተና ትጠፋለች። የትግራይ ሕዝብ፣ ጣሊያኖች ፋሽትን እንደደመሰሱትን ሙሶሊኒን ዘቅዝቀው እንደ ሰቀሉት፣ ወያኔን አውድሞ፣ ኢትዮጵያዊ የታሪክ ቦታውን መልሶ በእጁ እንደሚያስገባ ምንም ዓይነት ጥርጥር አይኑረን። በትግራይ ሕዝብ ኢትዮጵይዊነት ላይ ብቻ ዕምነት ይኑረን። የጊዜ ጉዳይ ነው! ሲነጋ ሲል ይጨልማል።

የሰላም አምባሳዶሮች ዛሬ፣ የሕዋሐት የጦር አበጋዞች ከሚያስለቅሷት የአፋር ክልል ደርሰዋል። መልካም ዕድል እንዲገጥማቸው እንመኝላቸውለን።

ኢትዮጵያችን ለዘለዓለም ትኑርልን!

[1] https://www.facebook.com/voaamharic/videos/424116394790927/

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here