ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓብይ አህመድ በአውሮፓ በኢትዮጵያ ኤምባሲዎች የተሰገሰጉትን አሻጥረኞች የዲሞክራሲ ጠላቶች ይመንጥሩልን

0
249

Ethiopian Embassy in Berlin.

Ethiopian Embassy in Berlin.

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓብይ አህመድ

እኛ በአውሮፓ የምንገኝ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በአገራችን በኢትዮጵያ የተጀመረውን የለውጥ ጉዞ እየደገፍን እና እያበረታታን በመቀጠልም በአገራችን በሚካሄደው የዲሞክራሲ ግንባታ የሰባአዊ መብት መከበር እንዲሁም የሃገር ግንባታ ለመሳተፍ በከፍተኛ መነሳሳት ላይ ብንሆንም
በተንኮል የታነጹት በአየር ባየር ንግድ የተጠመዱት ኢትዮጵያውያንን ሲሰድቡ ሲያሰድቡ ሲሰልሉ ሲያሰልሉ ሲጠቁሙ እና ሲያስጠቁሙ የነበሩ የኢትዮጵያ ህዝብ እየተራበ አገራችን ኢትዮጵያ በሌላት የውጭ ምንዛሪ እየተከፈላቸው ምንም ሳይሰሩ ኢትዮጵያውያንን ሲከፋፍሉ የኖሩ ያሮጌው ዘመን ቁማርተኞች ተላላኪዎች እና አሻጥረኞች በአውሮፓ ከሚገኙት የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች የተሰገሰጉ አሻጥረኞች የዲሞክራሲ ጠላቶችን ሙሉ በሙሉ ይመንጥሩልን።

ስራቸው እየዞሩ ኢትዮጵያውያንን መከፋፈል እንዲሁም ያየር ባየር ንግድ እና የሌብነት ስርዐት እንዲጧጧፍ ያደረጉ ኢትዮጵያውያንን ሲከፋፍሉ ሲያመናጭቁ እና ሲያሸማቅቁ የነበሩ ተግባራቸው እየዞሩ ካደራጁዋቸው ግብረዓበሮቻቸው ጋር እድር እና ሰንበቴ ሲበሉ የከረሙ በአውሮፓ የኢትዮጵያ ኤንባሲዎች የተሰገሰጉ አሻጥረኞች አምባሳደር ካውንስለር እና የዲያስፖራ ክፍል ተብዬዎችን ይመንጥሩልን።

እነዚህ በአውሮፓ የኢትዮጵያ ኤንባሲዎች ኢትዮጵያውያንን ሲያንገላቱ የነበሩ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሰራተኞች በሰሩት ሻጥር ግብረዓበሮቻቸውን በመሰብሰብ ብዙሃኑን ለሃገራቸው ቅን አሳቢ ኢትዮጵያውያንን ለስሙ በመጥራት በዋናነት ግን በማግለል በቅርቡ እ.አ.አ October 31 2018 በፍራንክፈርት ጀርመን እርስዎን ለመቀበል ከእርስዎ ጋር ለመወያየት በጉጉት ይጠብቁ የነበሩትን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ኢትዮጵያዊያን ወደ ዘግጅቱ ቦታ እንዳይገኙ አድርጓል የተገኙትንም አጉላልቱዋል አሳዝኖዋል አበሳጭቶዋል። ይህ ባይሆን ኖሮ የዝግጅቱ ቦታ ጠቦ ኢትዮጵያውያን ውጭም ቆመው በደስታ በተቀበልዎት ነበር።

በቀጣይነት እኛ በአውሮፓ የምንገኝ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሃገራችን ጉዳይ ሙሉ በሙሉ እና ቀጥታ ተሳትፎ ማድረግ እንድንችል ኢትዮጵያውያን በማሳደድ በመሰለል እና በመከፋፈል የሃገር ዘራፊዎችን ሲያስተናግዱ ሲያገለግሉ እና ሲገለገሉ የኖሩ በድህነት ከሚሰቃየው ህዝባችን ጉሮሮ ተነጥቆ በሚከፈላቸው የውጭ ምንዛሪ ሃገራቸውን እና ህዝባቸውን የበደሉ የሃገር ጠቃሚ ሳይሆን ጫና የሆኑትን ችሎታ ቢሶች አሻጥረኞች የዲያስፖራ ጉዳይ ሃላፊ እና ካውንስለር ተብዬዎች ጠራርገው ያጽዱልን።

አሁንም በአውሮፓ የምንገኝ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሃገራችን ጉዳይ ላይ አዎንታዊ ሚና እንዳይኖረን በማግለል በመጠራጠር በግፍ ዘመን ከኤምባሲው ጋር ሲሞዳሞዱ ከነበሩ ያሮጌው ዘመን ቁማርተኞች እጅ ነሺዎች ጋር ተቆራኝቶ የሚሰራውን የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች በአውሮፓ ያጽዱልን።

አሳዳጅ እና ተሳዳጅ ተጠርጣሪ እና ተገላይ በሆነ ስነ ልቦና ላይ በተመሰረተ ግንኙነት ባገራችን ጉዳይ መሳተፍ ስለማንችል በመተማመን የተጀመረው የለውጥ ጉዞ እንዲሳካ ሲጀመር ስነልቦናቸው በመተማመን ሳይሆን በመጠራጠር እንዲሁም ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በማሰባሰብ ሳይሆን በመከፋፈል ሴራ ላይ የተካኑትን እንዲሁም ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሲያጉላሉ እና ሲያሰቃዩ የነበሩትን አሻጥረኞች የኢትዮጵያ ኤምባሲ አባሎች በአውሮፓ ካሉት የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች በአፋጣኝ ያጽዱልን።

ከአክብሮት ጋር
የለውጡ ደጋፊዎች
በአውሮፓ የምንገኝ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here