እነ “እሽ አትበሉኝ የሹም ዶሮ ነኝ” ምን እያሉ ነው? (ይሄይስ አእምሮ)

0
23

ይሄይስ አእምሮ

Debretsion Gebremichael, Tigray Regional State President.

Debretsion Gebremichael, Tigray Regional State President and leader of Tigray Peoples Liberation Front (TPLF).

እኛ ኢትዮጵያውያን በየቋንቋችን እጅግ ማለፊያ የሆኑ አባባሎች አሉን፡፡ እስኪ እነዚህን ለአብነት ያል እንመልከት፡-

በፊት ነበር እንጂ መጥኖ መደቆስ፤

አሁን ምን ያደርጋል ወጪት ጥዶ ማልቀስ፡፡

አይነጋ መስሏት “ቋቷን አበላሸች”፡፡

እናቱ ወንዝ የወረደችበትና የሞተችበት እኩል ያለቅሳሉ፡፡

የማይቀጡት ልጀ ሲቆጡት ያለቅሳል፡፡

ወያኔዎች ያላሰቡት ዱብ ዕዳ ወርዶባቸው ይሠሩትን አጥተዋል፡፡ ትግራይን ከመጥፎ ንግርቶች ለማዳን የተያዘውን ብሔራዊ ጥረት ለማኮላሸት ዘርፈ ብዙ ጥረት እያደረጉ ይመስላሉ፡፡ በጥንካሬያቸው ዘመን እንዳሉ ለማስመሰል በተቆጣጠሩት ሚዲያ የማይዘባርቁት ነገር የለም፡፡ ትግርኛ የሚሰማ የሌላ ወገን ዜጋ ያለም አልመሰላቸውም፡፡ ይወቁት – እየተከታተልናቸው ነን፡፡

በትናንትናው ምሽት የዜና ዕወጃቸው ትግራይ ቲቪ አንዳንድ የትግራይና በጉልበት የተወሰዱ የበፊት የአማራ ከተሞችን ሰዎች እያነጋገረ ነበር፡፡ ማፈርን የማያውቁት ወያኔዎች የለውጡን ኃይል ከትግራይ ሕዝብ ጋር ለማላተም በጀመሩት ዘመቻ እነሱ በህግ ስም ያደርጉት ከነበረው ወንጀልና የግፍ ተግባር ሊወዳደር ቀርቶ ከመለስተኛ ወቀሳ ውጪ በጥፋተኝነት ሊያስወነጅል የማይችልን ጥቃቅን ነገር እያጎሉ ማቅረባቸውን ተያይዘውታል፡፡ ወያኔዎች በላብራቶሪ ውስጥ ወንጀል ፈልስመው ለንጹሓን ምሥኪን ዜጎች እንዳላደሉ፣ በሙስና የተዘፈቅን ሰው ዕኩይ የንቅዘት ተግባር በመያዣ ይዘውና ሆዳሞችን በገንዘብ ገዝተው ምሥክር በማሰልጠን በንጹሓን ላይ እንዳላቆሙ፣ ዜጎችን በማንነታቸው ብቻ እየለዩ ዘር እንዳይተኩ እንዳላመከኑና በበሽታና በመርፌ እንዳልጨረሱ፣ በጥላቻ ታውረው በተለይ አማሮችን በግብረ ሶዶም በቁማቸው ለመግደል 27 ዓመት ሙሉ እንዳልማሰኑ፣ አሁንም ቢሆን በመላዋ ትግራይ በሚገኙ ግልጽና ድብቅ የመሬት ውስጥ እሥር ቤቶች አማሮችንና የመከላከያ አባላትን ጭምር በማንአለብኝነት ጥጋብ ተወጥረው በብዛት አጉረው እንደማያሰቃዩ፣ የሀገራችንን አንጡራ ሀብት በጠራራ ፀሐይ አጓጉዘው ትግራይን በተዘረፈ ሀብት እንዳላጥለቀለቁ፣ በጥቅሉ ሰማይና ምድር የማያውቋቸውን ወንጀሎችና ኃጢኣቶች በኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ላይ እንዳልፈጸሙ … የለውጡ ኃይል ግልጽ የሀገር ሀብት ዘራፊዎችን “ለምን አጋለጠ፣ ለምንስ በቲቪ መስኮት በሰንሰለት አስሮ አሳየብን፣ ለምን ጉዳችንና ገመናችን ይፋ ይደረጋል?” ከሚል የቂሎች ፈlK=ጥ በመነሳት ቡራከረዩ እያሉ ነው፡፡ ከዱሮውም ሀፍረትን ስለማያውቁ አይፈረድባቸውም፡፡

ተጠርጣሪ ወንጀለኛ በሰንሰለት ታስሮ ወደ ማረፊያ ቤት መግባትም ሆነ በሚዲያ መታየት አዲስ ነገር አይደለም፡፡ የየትኛውም ሀገራት መሪዎችና ታላላቅ ባለሥልጣኖች በፖሊስ ሲያዙ እንደዚሁ ነው የሚደረገው፡፡ ትግራይ ላይ ሲመጣ የተለዬ ሊሆን አይችልም፡፡ የብራዚሉ መሪ፣ የጣሊያ መሪዎች፣ የጃፓን መሪዎች፣ የደቡብ ኮሪያዋ መሪ፣ ወዘተ. ሲያዙ በእጅ ብረት ተጠርንፈው ነው ወደ ዘብጥያ የወረዱትና የሚወርዱትም፡፡ ጄኔራል ክንፈ ዳኘው ምን ስለሆነ በወታደራዊ አጀብና በመድፍ ተኩስ ታጅቦ በክብር ወደ እስር ቤት እንደሚገባ የሚያውቁት ወያኔዎች ብቻ ናቸው፡፡ ከደነቆሩ አይቀር እንደዚህ ነው – ከልደት እስከሞት፡፡ “በቅሎ ‹አባትሽ ማን› ቢሏት ‹እናቴ ፈረስ› ነች” አለች እንዲሉ ማጣፊያው ሲያጥራቸው ነገሩን ወደ ጎሣ ፖለቲካ አዙረው “ትግራይን  ለማንበርከክ ነው እንዲህ የሚደረገው” አሉና ዓለምን አስደመሙት፡፡ የክንፈ “ወንጀል” በምን ሂሣብ ነው የትግራይ ወንጀል ሊሆን የመችለው? “አሁን ነው መሸሽ” እንግዲያውስ፡፡ ይህ ታሪክ የአያ ጅቦን ነገር ያስታውሰናል፡፡ ብቻውን ሲለቆምጭ ከርሞ የኋላ ኋላ አደጋ ሲመጣበት ልጆቹ እንዲረዱት ይጠይቃቸዋል፡፡ እነሱ በምን አበሳቸው፡፡ “ብቻህን እንደባለህ ብቻህን ቻለው” አሉታ! ትግራይ ትወቅበት፡፡

ይገርሙኛል፡፡ ወያኔዎች በጣም ይገርሙኛል፡፡ መማር ሲያልፍ የማይነካቸው፣ ማደግና መለወጥ የተጠየፋቸው፣ እንደችፍርግ እዚያው ባሉበት መዝለቅን የመረጡ፣ እንደካሮት ወደታች እንጂ እንደሸንበቆ ወደላይ መመዘዝን የሚጠሉ፣ ማገናዘብ ዕርም የሆነባቸው፣ ሰው መሆን የሚናፍቃቸው እነዚህ ጉዶች “እንደተወለዱ ሞቱ” ቢባል የሚያንሳቸው እልም ያሉ ደንቆሮዎች ናቸው፡፡

ሌላው በትናንትናው ዜና የገረመኝ ትግራይንና ሕዝቧን እንደወከሉ ተደርጎ የቀረቡት ዜጎች የተናገሩት ነገር ነው፡፡ በታሰሩት ሰዎች ላይ ዶኩመንታሪ ተሠርቷል መሰለኝ፡፡ እንደዚያ ሆኖ ከሆነ ስህተት ነው በርግጥ፡፡ ከወያኔ አንጻር ግን ይህን ነገር ለመቃወም ትግራይና ተጋሩ የመጀመሪያ ሊሆኑ አይችሉም፤ አይገባምም፡፡ ኧረ እጅግ ያሳፍራል፡፡ ተጋሩ የት ከርመው ነው ዛሬ ለተቃውሞ የተነሱት? አማራው እየተገደለ ወደ ገደል ሲጣል የት ነበሩ? አማራው ላይ ያ ሁሉ ሊሰሙት የሚዘገንን ግፍና ስቃይ ሲደርስ እነዚህ “ለሰው መብት ተቆርቋሪ” ትግሬዎች የት ነበሩ? ወይንስ የሰው ግርድና አመሳሶ አለው? እንደዚያ ያለ ነገር የማውቀው በአይሁዶችና በኢ-አይሁዶች ነው፡፡ ዝርዝሩ ብዙ ስለሆነ ወደዚያ አሁን አልገባበትም፡፡  ሕወሓት ለ27 ዓመታት ያን ሁሉ ሰማይና ምድር የማይችሉት ዘረፋና ቅጣ ያጣ ግፍና በደል በኢትዮጵያውያን ላይ ሲፈጽም እነዚህ ትናንትና ትከሻቸውን እየሰበቁና “እናሳያቸዋለን! ጦርነትን እንኳን መዋጋት ጠፍጥፈን እንሠራዋለን” በሚል የቆዬ ዕብሪት  ለጂኒራር ክንፈ የተከራከሩት ትግሬዎች እስከዛሬ የት ተደብቀው ነበር? ድምፂ ወያኔና ትግራይ ቲቪስ በአማሮች ላይ የደረሰውን ስቃይና በደል በሌሎች ሚዲያዎች እየሰሙ ለምን ጆሮ ዳባ ብለው አለፉት? የአማራ ነፍስ ከዶሮ ነፍስ ታንስ ይሆን? ወያኔ የሚፈጽመውን ሰቆቃ እንደ ጽድቅ፣ በወንጀለኛ ወያኔዎች ላይ የምትደርስን ትንሽዬ የሚዲያ ሽንቆጣ ግን እንደታላቅ ድፍረትና ወንጀል መቁጠር ከምን የመነጨ ይሆን? “እኛ አዛዥ ናዛዥ ስለሆንን ማንም ሊደፍረን ቀርቶ ዝምባችንን እሽ ሊለው አይገባም” ለማለት ይሆን? አዎ፣ “እሽ አትበሉን የሹም ዶሮዎች ነን” ማለት አሁን ነው፡፡ አዎ፣ “የማይቀጡት ልጅ ሲቆጡት ያለቅሳል ማለት አሁን ነው፡፡ …

እንግዲያውስ ገና ምኑ ታየና! የሚታየንን ሁሉ የማንናገር ሞኞች አለን፡፡ እኔም ሞኝ ነኝ፡፡

ግን ይሄ “ሌላውም ይታሰር” የሚሉት ነገር አልገባኝም፡፡ አንደኛ ሌላውም እየታሰረ ነው፤ ትግሬ ተለይቶ የታሰረበት ሁኔታ የለም፡፡ ሁለተኛ ከሚታሰሩት አብዛኛዎቹ ትግሬ ቢሆኑ ከቅርብ ጊዜው ሸፋፋ ታሪካችን አንጻር አያስገርምም፡፡ ወያዎች ከጥቂት አንጎለቢስ ሆዳሞች ጋር ሆነው  ጋር በበሉት ሌላው አማራና ኦሮሞ ምን ቤት ነኝ ብሎ ነው እስራታቸውን የሚጋራው? ሌላው ቆሞ ለተመለከተ፣ ከቶውንም ላልበላበት ነገር መናጆ መሆን አለበት እንዴ? 27 ዓመት ሙሉ ትግሬ ለትግሬ እየተጠራራች ከነቤተሰቧ ልቁምጭ አድርጋ  በበላች አሁን ደርሶ ለመከራው ሲሆን ሌላውም ጎሣ ይያዝልኝ ብሎ መደንፋት ምን የሚሉት ፈሊጥ ነው?

አንድ ነገር ትዝ አለኝ፡፡ ትናንት ማታ የጂኒራር አበበ ተ/ሃይማኖትን የዋልታ ቲቪ ቃለ ምልልስ በከፊል ተከታተልኩ፡፡ በነገራችን ላይ ወያኔ የቁም ስቅላቸውን ካበላቸው ነገሮች መካከል ቃላትና የማዕረግ ስሞችም በዋናነት ይጠቀሳሉ፡፡ ከነዚህም መካከል ኮሎኔል፣ ብ/ሜ/ሌ/ጄኔራል፣ ዶክተር፣ ዴሞክራሲ፣ ነፃነት፣ሰላም፣ ፌዴራል መንግሥት፣ ህገ-መንግሥት የሚሉት ዋና ዋናዎቹ ናቸው – እንዴ፣ የአራተኛ ክፍል ደካማ ምሩቅ ሙሉ ጄኔራልና በድራቦሹም ፕሮፌሰር የሚኮንባት ብቸኛ ሀገር እኮ ናት ኢትዮጵያ! ስንገርም፡፡ ወያኔ እንዴት እንዳዋረደን መቼስ … ፡፡  እናላችሁ ይህ ሰውዬ፣ ይህ ጂኒራር ተብዬ ለማያውቁት ሲታጠንላችሁ “የአዲሱ መንግሥት የፓርላማ አባላት የዶ/ር ዐቢይ ‹ራበር ስታምፕ› ናቸው” ብሎ ዕርፍ አይል መሰላችሁ፡፡ እንደውነቱ ብዙ ነገር ትክክል ብሏል – ለሰይጣንም ቢሆን የሚገባውን አለመከልከል ደግ ነው፡፡ ግን በዳዴ እየሄደ ያለና እርሱና ወንድም እህቶቹ ለ40 ምናምን ዓመታት ያግማሙትን ሀገራዊ ጉዳይ በግማሽ ዓመት ምን ያድርጉት ሊል እንደፈለገ አልገባኝም፡፡ እርሱ የባዶ ስድስት ኃላፊ እያለ ያሰቃያቸውንና የገደላቸውን ዜጎች ከምን ጊዜው ረስቶ እንዲህ የዴሞክራሲ ጠበቃ ሊሆን እንደቻለም አልገባኝም፡፡ የሆኖ ሆኖ አቤ ጆቤ ወንድሞቹ አደጋ ውስጥ የገቡ በመሰለው ቁጥር በሚዲያ ብቅ እያለ ዋስ ጠበቃና ተከራካሪ ሊሆንላቸው መፈለጉን አልቃወምም፡፡ ግን ግን ከሚጠቅሰው የወንድሞቹ ሀገራዊ የዕድገትና ብልግና ማለትም ብልፅግና በተጓዳኛ እነዚሁ የብዔልዘቡል አሽከሮች ወንድሞቹ በሕዝቡና በሀገሪቱ ላይ ያደረሱትን በመቶዎች ዓመታት ሊጠገን የማይችል ቁሣዊና መንፈሳዊ ኪሣራ በተመለከተ ትንሽ ቢተነፍስ በወደድኩለት፡፡ “ክርስቶስ ለሥጋው አደላ” እንደሚባል ይህ ሰውዬ ለጨፍፊ ወንድሞቹ ያለውን አዘኔታ ከመግለጽ ባለፈ ለተጎዳው ሕዝብ ማሰቡን ያስረዳበት የሃሳብ ይዘት በጣም ደካማ ነው፡፡ ይልቁንም የወንድሞቹን ገመና ለመሸፈን የሄደበት ርቀት በዝቶ ታይቶኛል – እንደኔ፡፡ ነገር ደግሞ እንደተመልካቹ ነው፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here