አዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ አካባቢዎች ያለበቂ ምክንያት ብጥብጥ የሚፈጥሩ አካላት ከተግባራቸው እንዲቆጠቡ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አስጠነቀቀ

0
32

መስከረም 03፣2011

የፊታችን ቅዳሜ ወደ አገር ቤት የሚገቡ የኦነግ አመራሮችን ለመቀበል የሚደረገው ዝግጅት በሰላም እንዲጠናቀቅ ፖሊስ በቂ ዝግጅት ማድረጉን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል አቶ ዘይኑ ጀማል ገለጹ።

ኮሚሽነሩ ለኢቢሲ በሰጡት ማብራሪያ እንደገለጹት በአንዳንድ የአዲስ አበባ አካባቢዎች የኦነግን አርማ በሚሰቅሉና በአዲስ አበባ ወጣቶች መካከል ግጭቶች መከሰታቸውን ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ወጣቶች አርማቸውን ይዘው የሚመጡ ወጣቶችን የመከልከልም ሆነ የመፍቀድ ሀላፊነት የፖሊስ በመሆኑ አርማ የሚሰቅሉ ወጣቶችን መከልከል የለባቸውም ያሉት ኮሚሽነሩ የኦነግን አርማ በየአካባቢው የሚሰቅሉ ወጣቶችም የህዝብ መገልገያ የሆኑ አውራ ጎዳናዎችንና ፖሎችን ቀለም ከመቀባት መቆጠብ አለባቸው ብለዋል።

መኪና የመስበርና ድንጋይ የመወርወር፣ ተቀጣጣይ ጋዝ ይዞ ፖሊስ ጣቢያዎችን ለማቃጠል የመሞከር አዝማሚያዎች እየታዩ መሆኑን የገለጹት ኮሚሽነሩ ማንም ሰው ጉልበተኛ ነኝ ብሎ በህዝብ ላይ፣ በአገር ተቋማት ላይ ጉዳት ሲያደርስ ፖሊስ ህግን የማስከበር ስራ እንደሚሰራ ገልጸዋል።

አርማ ይዞ መውጣት ፖሊስ አልከለከለም፣ ማንማ ሰው የራሱን አርማ ይዞ በሰላማዊ መንገድ እስከተንቀሳቀሰ ድረስ ምንም ጉዳት እንደሌለውም አቶ ዘይኑ ጀማል አስታውቀዋል።

የፊታችን ቅዳሜ ወደ አገር ቤት የሚገቡ የኦነግ አመራሮችን ለመቀበል የሚደረገው ዝግጅት በሰላም እንዲጠናቀቅ ፖሊስ በቂ ዝግጅት ማድረጉንም አቶ ዘይኑ ገልጸዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here