ባለስልጣናቱ ሰላማዊ ሰልፍ በመውጣታቸው የተገደሉ ዜጎችን በሀሰት እየወነጀሉ ነው

0
24

Ethiopian officials speaking on current issues.

በአዲስ አበባ ዙሪያ የተፈጸመውን በዘር ላይ የተመሰረተ ጭፍጨፋ ለመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ የወጡ ቢያንስ 5 ሰዎች በወታደሮች ተገድለዋል፣ ከ12 በላይ ሰዎች ቆስለው ሆስፒታል ገብተዋል። ግድያው የተፈጸመው የመንግስት አካላት በአዲስ አበባ የተካሄደውን ሰላማዊ ሰልፍ ለማስተጓጎል በመፈለጋቸው መሆኑን የተለያዩ የመረጃ ምንጮች ያመለክታሉ። ይሁንና ባለስልጣናቱ ግድያው አግባብ እንደሆነ ለማስረዳት የሚጣረሱ ምክንያቶችን በመደርደር ላይ ናቸው።

በሚያሳዝን መልኩ ልክ በወያኔ ጊዜ ሲደረግ እንደነበረው የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄኔራል ዘይኑ ጀማል “የተገደሉት ሰዎች ከወታደሮች ላይ መሳሪያ ሊነጥቁ ሲሉ” በቀጥታም ባይሆን በገደምዳሜ “ዘረፋ ሊፈጽሙ ሲሉ…” በማለት በወገኖቻቸው ላይ ጭፍጨፋ መፈጸሙን በመቃወም አደባባይ በመውጣታቸው ምክንያት በግፍ የተገደሉ ዜጎችን በሀሰት ወንጅለዋል።

የኢትዮጵያ ጠቅላይ አቃቢ ህግ የኮምንኬሽን ሀላፊ አቶ ታዬ ደንደአ በበኩላቸው ኮሚሽነር ዘይኑ ጀማል ከተናገሩት በሚጣረስ መልኩ ሰላማዊ ሰልፈኞቹን ሲወነጅሉ እንዲህ ብለዋል:-

አሁን ጥያቄው ግልፅ ሆኗል “የኦሮሚያ መንግስት ከአዲስ አበባ ይውጣ! ታከለ ኡማ ከስልጣን ይውረድ! የሽግግር መንግስት ይመስረት! ብሔር ይጥፋ!”
በአዲስ አበባ ሰልፍ ላይ ተሰምቷል። ይሄ የጋሞ ህዝብ ጥያቄ ነው ተብለናል። በጣም ጥሩ ነው!
በቅርቡ መልስ ያገኛል!

አቶ ታዬ ደንደአ ሰላማዊ ሰልፈኞቹ ያላሉትን ሆን ብለው ለውንጀላ በሚያመቻቸው መልኩ ከማቅረብም አልፈው በህዝብ ላይ ዛቻ ሰንዝረዋል።

የአዲስ አበባ ህዝብ ሙሉ በሙሉ ሰላማዊ በሆነ መንገድ አደባባይ ወጥቶ በወገኖቹ ልይ የተፈጸመውን ጭፍጨፋ ማውገዙ ለምን የመንግስት ባለስልጣናትን እንዳስቆጣና ሰላማዊ ሰልፈኛው ላይ ተኩስ አስከፍተው ግድያ እንዳስፈጸሙ ግልጽ አይደለም።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here