በዚምባብዌ የተካሄደውን ምርጫን ተከትሎ ግጭት ተቀሰቀሰ

0
5

በዚምባብዌ የተካሄደውን ምርጫን ተከትሎ ግጭት ተቀሰቀሰ
**********************************************
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በዚምባብዌ የተካሄደውን ምርጫን ተከትሎ የተቀሰቀሰው ግጭት እንዳሳሰባቸው የድርጅቱ ዋና ጸሀፊ አንቶንዮ ጉቴሬዝ ገለጹ።
የዚምባብዌ ፖለቲከኞች ግጭቱን እንዲያስቆሙም ጠይቀዋል።
የብሪታንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ግጭቱ እንዳሳሰባቸው ገልጸው የአገሪቱ ፖለቲከኞች ግጭቱን ለማስቆም በሀላፊነት እንዲሰሩ ጠይቀዋል።
የዚምባብዊ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤ ከስልጣን ከለቀቁ ወዲህ በተደረገው የመጀመሪያው የምርጫ ውጤት የዚምባብዌ ገዢ ዛኑ ፒ ኤፍ ፓርቲ ማሸንፉ ተገልጿል።
የዚምባብዌ ምርጫ ኮሚሽን ዛኑ ፒ ኤፍ ፓርቲ 140 ወንበር በማግኘት ማሸነፉ ይፋ አድርጋል።
የተቃዋሚው ኤም ዲ ሲ አሊያንስ ፓርቲ ደግሞ 58 ወንበር ማግኘቱን ገልጿል።
የምርጫ ውጤት መገለጹን ተከትሎ ለተቃውሞ በወጡት ዜጎች ላይ የመንግስት ወታደሮች አስለቃሽ ሽጭስ መተኮሳቸውንና ሶስት ሰዎች መሞታቸው ተነግሯል።
ምንጭ፣ ቢቢሲ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here