ለመጀመሪያ ጊዜ ወታደራዊ ስልጠና የወሰዱ ዲፕሎማቶች ተመረቁ

0
80


ለመጀመሪያ ጊዜ ወታደራዊ ስልጠና የወሰዱ ዲፕሎማቶች ተመረቁ

በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የ110 ዓመት ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ወታደራዊ ስልጠና የወሰዱ ዲፕሎማቶች ተመረቁ፡፡

የኢ.ፌ.ዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ፣ በሆለታ ገነት በሚገኘው ሜጀር ጀኔራል ሀይሎም አርአያ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ማዕከል ውስጥ ለአንድ ወር ያህል ወታደራዊ ስልጠና የወሰዱትን 4ኛ ዙር ሰልጣኝ ዲፕሎማቶች በቦታው ተገኝተው መርቀዋል፡፡

ያለንበት ጊዜ ሀገራቸውን የሚወዱ፣ንቁና ትጉህ፣ በዲሲፕሊን የታነፁ፣ ተለዋዋጭ የሆነውን የአካባቢያችንና የአለምአቀፍ ዲፕሎማሲያዊ ሁኔታ በጥልቀት የሚረዱ ዲፕሎማቶች ለሀገራችን የሚያስፈልግበት ጊዜ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

ከሀምሌ 15 ቀን ጀምሮ ስልጠናውን ወስደው በስኬት ያጠናቀቁት ሰልጣኝ ዲፕሎማቶች 89 ሲሆኑ ከእነዚህም ውስጥ 34ቱ ሴቶች መሆናቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here