ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከልና ለመቆጣጠር መንግስት ህጋዊ የውጪ ሀገራት የስራ ስምሪት ስራዎች ወደስራ ሊያስገባ ይገባል ተባለ

0
75


ህጋዊ የውጪ ሀገራት የስራ ስምሪት ስራዎች
ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከልና ለመቆጣጠር መንግስት ህጋዊ የውጪ ሀገራት የስራ ስምሪት ስራዎች ወደስራ ሊያስገባ ይገባል ተባለ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ጄኔቫ ግሎባል ከተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር ከህጋዊ የውጪ የአሰሪና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ጋር በመሆን በስራ ስምሪት ደህንነት ዙሪያ የምክክር መድረክ አካሂዷል፡፡

በውይይቱ ላይ እንደተገለፀው በከተማዋ የውጪ ሀገራት የአሰሪና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ ባለቤቶች ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላካከልና ለመቆጣጠር ህጋዊ የውጪ ሀገራት የስራ ስምሪት ስራዎችን ማመቻቸት ይገባል ተብሏል።

ለህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር መባባስ አስተዋፅኦ የሚያደርጉ የመንግስት መዋቅር አካላትም ከድርጊታቸው ሊታረሙ እንደሚገባ ነው የተገለጸው፡፡

በህጋዊ መንገድ የሚደረጉ የውጪ ሀገራት የስራ ስምሪቶች ዜጎችን ተጠቃሚ ከማድረግ ባሻገር ለሀገር የውጪ ምንዛሪ በማስገኘት ረገድ አስተዋጽኦ እንደሚያደርግም ተጠቁሟል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አማካሪ ቦርድ ጽህፈት ቤት ሃላፊና የስራ ስምሪት አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ካሳ ስዩም የውጪ ሀገራት የስራ ስምሪት ህጋዊነቱን ተከትሎ እንዲሰራ ለማስቻል ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ምክክር ማድረግ ማስፈለጉ መግለጻቸውን የአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ዘግቧል..#EBC

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here